Smiley face

አንቀፅ 39 ይደመርል!

ላንት አብዲ ኢሌ ያስነሳውን አዋራ መከላከያችን ባጥጋቢ ሁኔታ ያበረደው መሆኑን አይተናል፡፡መከላከያ ከጎሳ ፖለቲካ ከወጣና በስብጥሩም “ደብረጽረጽ” ያለ የብሄር ተዋጽኦ ካለው ማንም ምንም እንደማያመጣም አሳይቶናል፡፡ይህን አጋጣሚ ግን በቀላሉ እንድናልፈው አልፈለኩም፡፡ ነገስ ይሄ ሀገር አፍራሽ አካሄድ ላለመደገሙ ምን መተማመኛ አለን?! አሁን እንደምናየው ከሊቅ እስከ ደቂቅ “እኔ” እንጂ “እኛ” ማለት ከተወ ሰነባብቷል፡፡ሁሉም በየብሄሩ ግፋ ሲልም በየጎጡ መሸጎጥ ይዟል፡፡.. እኔ በበኩሌ ብሄር እና ጎሳ ይጥፋ ምናምን የሚል ዘፈን ውስጥ የለሁበትም፡፡…ምንም እንኳን ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተገኘሁ ብሆንም ኩሩ ..ያውም እጅግ በጣም ኩሩ ኦሮሞና ኢትዮጲያዊ መሆኔን አምኜ የተቀበልኩ ማንም ከእኔ ብሄር ያንሳልም ይበልጣልም ብዬ የማላምን ሰው ነኝ፡፡…ጥሎብኝ እቺ ኢትዮጲያ የምትባልን ሀገር አጥብቄ እወዳለሁ…በውስጧ ያሉትንም እያንዳንዳቸውን ብሄር ብሄረሰቦች እንደወንድምና እህቶቼ ያህል (ሰው በመሆናቸው መነሻ ምናምን ብዬ በመመጻደቅ ሳይሆን ኢትዮጲያዊ ስለሆኑ ብቻ ከሌላው የሰው ልጅ በለጥ አድርጌ) እወዳቸዋለሁ፡፡…አንዳንዴ በጊዜያዊ ፖለቲካ ከአንዳንዶች ጋር ስንናከስ ብታዩን የምርም የተጣላን ይመስል ይሆናል…ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ ይህን ፖስት ጽፌ ስጨርስ እና ስልኬን ሳበራ ከሚኖሩኝ አምስት “የተደውሎሎት ነበር” መልእክቶች ሶስቱ የተጋሩ 2ቱ የነፍጠኛ ጓደኞቼ ነው ..ሎል፡፡እንግዲህ ዚስ ኢዝ ዘ ሪያሊቲ፡፡አሁን አሁን ግን ኢትዮጲያውያን አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ጥቂቶች በመሰሪነት ባበጁልን የጥላቻ መንገድ መፍሰስ ከቀጠልን ወደፊት እንደሀገር ለመኖር መቻላችንንም እየተጠራጠርኩ መጥቻለሁ፡፡ ለምሳሌ እኔ እና ጓደኞቼ ባጋጣሚ በከፍተኛ ደረጃ የተማርን በመሆናችን(ትንሽ ጉራማ ያስፈልጋል..ሎል) እርስበርሳችን አንደኛው ባንደኛው ብሄር ላይ እስከሚበቃው እየቀለደ አንዱ አብንን ሌላው ኦነግን አንደኛው ግ.7 ን አንዱ ህወሃትን …ዚስ ዴይስ ደግሞ አብይን እየደገፈ ወይም እየነቀፈ ስንጨቃጨቅ ቆይተን መለያያችን ሲደርስ ያለምንም ጠብ ተቃቅፈን እንለያያለን፡፡ይህ ግን ለሁሉም ይሰራል ማለት አይደለም፡፡…አትድረስብኝ አልደረስብህም በዝቷል….ግፋ ሲልም ወደ መገዳደልና በቆንጨራ መጎራረድም ጀምረናል፡፡ …..በአዋሳ እኮ የሟለ ህጻናት መመህር ሰውን ለማቃጠል ክብሪት እየለኮሰች የሚያሳይ ቪዲኦ ካየን ገና ወር አልሆነንም፡፡ ..መሃይም የወረዳ እና የዞን አመራሮች በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ያደረጉትንም አይተናል፡፡ ባስ ሲልም እንደ አብዲ ኢሌ አይነቱ ፍልጥ መሃይም ድንገት በአንደኛው ቀን ተነስቶ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አሳይቶናል፡፡
ስለዚህ ምን እናድርግ….!?
ወሬ ይዤ ዝም ብዬ ረሳሁት እንጂ የዛሬ ዋና ርእሴ ይሄ አይደለም፡፡ይህንን እመለስበታለሁ፡፡ዛሬ በዋናነት የማነሳው ሃሳብ አንቀጽ 39 ን የሚመለከት ነው፡፡….እንደኔ እንደኔ መለስና ጓደኞቹ በህገመንግስታችን ላይ የራስን እድል በራስ ስለመወሰን እና ራስን ስለማስተዳደር ማካተታቸው በእውነት በግዜው ከነበረው እውነታ አንጻር ሸጋ ነበር፡፡…የፌዴራል ስርአቱ እና አደረጃጀቱ ላይ ግን ረጋ ተብሎ ያልታሰበባቸው ህዝብም በሙሉ አቅሙ ያልተወያየባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡..ከእነዚህም አንዱ ዋንኛው እና ዝነኛው የብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠል የሚለው አንቀጽ ነው፡፡….
ወገኖቼ ሁላችሁም እንደምታውቁት ለባለፉት ሀያ ምናምን አመታት ይቺ እስከመገንጠል የምትለው ሃሳብ ከልጅ እስከ አዋቂ ስትብጠለጠል ቆይታለች፡፡በእርግጥ ከዚህ በፊት የነበረው መንግስት መስሚያው ጥጥ እንደነበረ እናውቃለን፡፡አሁን በመጠኑም ቢሆን የሚሰማ መንግስት መጥቷል ብዬ አምናለሁ፡፡ይህንንም እድል ተጠቅማ አዳሜ የማታነሳው ጥያቄ የለም፡፡መንግስትም ያቅሙን ያክል እየመለሰ ነው ማለት ይቻላል፡፡…እና እኔም ምን አሰብኩ ለዚህች እማማ ኢትዮጲያ የሚቆቁርላት ግሩፕ ኦልሞስት የሌለ በመሆኑ…ስለ ልሙጥ እና ኮከቡ ባንድራ ከምንከራከር ይልቅ (ይቅርታ አድርጉልኝና ጉዳዩ ዛት ማች ኢምፖርታነቱ አይታየኝም) ….. መንግስትም ከትንሽ ግዜ በኋላ ጆሮውን መድፈን ሳይጀምር ቶሎ ብለን በአንቀጽ 39 ላይ በተለይ ደግሞ “እስከ መገንጠል” የምትለዋን ብቻ ለይተን ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግባት(ሪፈረንደም) ግፊ እናደርግም፡፡
ደሞም ታስቡት …ቆይ አለም ሁሉ ደደብ ሆኖ ነው እኛ ብቻ ከ200 ምናምን አገራት ነቄ ሆነን” እስከመገንጠል “የሚል መብትን በህገመንግስት የምናካትተው …?!(“ሴንት ኪቲስ ኤንድ ኔቪስም” አለች እኮ እንዳትሉኝ ደግሞ !…የሁለት ደሴቶች ውህደት የሆነችና ሚጢጢ የህዝብ ብዛቷ ከኢትዮጰያ ቡና ደጋፊ የማይበልጥን ሀገር “እሷም አለች ብቻችንን አይደለንም” አይነት ክርክር አይነፋም!..ሎል)፡፡….
እና ካለኛ አዋቂ የለም…!? መልሱልኛ..!?
እራስን በራስ ማስተዳደር እንደፈለገ ይፈቀድ …..ኦሮሚያ ክልል ከፈለገች የፈለገችውን ታድርግ …የአሽከርካሪ ህግ ሁላ ቀይራ ቀኝ መሪም ትጠቀም ….የጊዜ ሰሌዳም ትቀይር …ያሻትን ታድርግ …የሞት ፍርድ በአንድ ክልል ኖሮ በአንድ ክልል አይኑር….በአንድ ክልል…..የቀን አቆጣጠር በግሪጎሪያን ሆነ በአንዱ ክልል እንደ ኢትዮጲያውያን አቆጣጠር ይባል..ከፈለገ…በአንዱ ክልል አብን በአንዱ ክልል ኦነግ..በአንዱ ክልል አረና..ወዘተ ስልጣን ይዘው ለህዝባችን ይበጃል ያሉትን ያሻቸውን ያድርጉ …የፈለገ …የፈለገ .ይሁን…ግን ይሄ ሁሉ መብት በኢትዮጲያዊነት ጣራ ስር ብቻ ይፈቀድ!
ልብ ካለን የቅዳሜው የአብዲ ኢሌ ግርግር በቂ መማርያ ሊሆነን ይገባል፡፡
እናም ፕሊስ ጆይን ሚ ዊዝ ….
#አንዱአለም እባላለሁ ፡፡ኩሩ ኢትዮጲያዊ ነኝ፡፡ በአንቀጽ 39 ላይ የተቀመጠውን የእራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እደግፋለሁ፡፡ነገርግን ይሄ መብት ከፌዴሬሽኑ እስከመገንጠል ድረስ የተለጠጠ መሆኑን የሚፈቅድ አንቀጽ በህገመንግስታችን ላይ የተካተተ መሆኑን አጥብቄ እቃወማለሁ!
#My name is Andualem. I am a proud Ethiopian. I still hold that having the right of self determination in our Constitution was the right move then. However, I strongly oppose the Inclusion of the right of secession from the Federation in the Ethiopian Federal Constitution.
እውነት እውነት እላችኋለው ይሄን በሁለት አመት ግዜ ውስጥ ካሳካን በዚህ ጉዳይ ላይ የተሳተፍን ሰዎች በሙሉ እራሳችንን…በካራማራ ለኢትዮጲያ አንድነት ከወደቁት ጀግኖች እንደአንዱ መቁጠር እንችላለን፡፡
ኢትዮጲያ ከነክብሯ እና ሙሉ አካሏ ለዘላለም ትኑር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *